=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
እውነተኛ መሆን አሏህ ዘንድ ተወዳጅ ምግባር ነው። ግልፅነትም የቀልብ ማፅጂያ ነው። ተሞክሮም ማስረጃ ነው። መሪም ቤተሰቡን አይዋሽም። ልብን በማረጋጋትና የላቀ ምንዳን በማስገኘት ከዚክር (አሏህን ከማውሳት) የተሻለ ስራ አልተገኘም።
--<({አልቁርአን 76:9})>--
«አስታዉሱኝ አስታውሳችኋለሁና።»
ጥራት የተገባውን ጌታ ማውሳትም ምድራዊ ጀነት ሲሆን ያልገባት ሰው የአኺራውን ጀነት አይገባትም። ነፍስንም ከሚፀናወቷት የድካም ፣ የጭንቀትና የመዛባት ስሜቶች ያላቅቃታል። እንዲያውም ወደ ስኬትና መድህን የሚመራ አቇራጭ መንገድ ነው። አሏህን ማውሳት የሚያስገኛቸውን ፋይዳዎች ለመገንዘብ ሰማያዊውን ራዕይ(ቁርአን) ያካተቱ መዛግብትን ማሰስ ትችላለህ። ፍቱን መድህንን ከሻህ ደግሞ ቀን ተሌት አጣጥመው።
ጥራት የተገባውን አሏህ በማውሳት የፍርሃት ፣ የድንጋጤ ፣ የጭንቀትና የሃዘን ደመናዎች ይበተናሉ ፤ የትካዜ የችግርና የቁጭት ተራሮችም ይናዳሉ። አሏህን አዘውትረው የሚያወሱ ሰዎች የህሊና እረፍትን ቢያገኙም አያስገርምም። ባይሆን እጅግ የሚገርመው እሱን ከማውሳት የተዘናጉ ሰዎች በህይወት መኖር መቻላቸው ነው።
--<({አል-ቁርአን 16:21})>--
«ህያው ያልሆኑ ሙታን ናቸው። መች እንደሚቀሰቅሱም አያውቁም።»
ህመም ተሰምቶህ ስሞታ የምታቀርበው ሆይ..... ስቃይ ደርሶብህ የምታለቅሰው ሆይ.... አደጋ አጋጥሞህ የደነገጥከው ሆይ.... አስከፊ ችግሮችም ያካበቡህ ሆይ.... በል በተቀደሰው ስሙ ተጣራ አምሳያም የለውም።
እሱን ባወሳህ ቁጥር ህሊናህ ያርፋል ፣ ልቦናህ ይረጋጋል ፣ ነፍስህም ትደሰታለች። ምክኒያቱም እሱን ማውሳት። በሱ መመካት ፣ በሱ መተማመንን ፣ በሱ ላይ ተስፋ መጣልን ፣ ወደ እሱ መመለስን ፣ ከሱ መልካምሙን ሁሉ መሻትን ፣ መፍትሄን ከሱ መጠበቅንም ያስገኛል። እሱ ቢለመን ቅርብ ነው ፤ ቢጠራ ሰሚ ነው ፤ ቢጠየቅም ሰጭ ነው። ስለዚህ ተናንሰህ ፣ ተዋርደህ ተዋደቅለት ፤ የተባረከውንና የፀዳውን ስሙን በምላስህ እየደጋገምክ አወድሰው ፤ አልቀው ፤ ለምነው ፤ ማርታንም ጠይቀው ደስታን ፣ ሰላምን ብርሃንን እና እርካታን ታገኛለህና።
--<({አልቁርአን 3:148})>--
«አሏህም የቅርቢቱን ምንዳና የመጨረሻይቱን መልካም ምንዳ ሰጣቸው።»
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|